ABBA BAHREY FORUM (ABF)

አባ ባሕርይ መድረክ (አ.ባ.መ.)


 

 

Welcome Home Away from Home



Welcome to the website of the Abba Bahrey Forum (ABF). We are a nonpartisan group of scholars and professionals committed to constructive, accountable civic engagement (see our self-description under 'Who We Are'). As a community of practice, we strive to promote all internationally recognized rights for citizens and groups, as well as the rule of law. Our inspiration comes from Abba Bahrey, a late sixteenth-century Ethiopian monk, scholar, and pedigreed historian of the Oromo.  We are inspired by his exemplary respect for reason and evidence.

 

ABF is committed to supporting Amara-focused organizations and those Ethiopianist ones with a proven record of promoting liberty, equality, justice, accountability, and national unity. Faithful to these principles, this website showcases public documents, press releases, calls, and recommended resource materials issued by various kindred rights-based civic organizations. 


Please visit us frequently for updates and uploads.  Thank you!


Launched: May 20, 2023.

  


₪     ₪     ₪     ₪    


 

 

እንኳን ደኅና መጡ!


አማራ = ነጻ ሕዝብ  * * *  አምሓራ = የነጻነት ምድር

 

አባ ባሕርይ መድረክ የራዕይና የመፍትሄ ምክረ ሃሳቦችን አፍላቂ የምርምር ስብስብ ነው።

እውቀትን፣ ምክኒያታዊነትንና ማስረጃዎችን መሠረት ያደረጉ ጥናቶቹ የአማራን ብሎም 

የኢትዮጵያ መብት ተኮር ድርጅቶችን የሚያጎለብቱ ናቸው ብለን እናምናለን።

 

 


ይህ “የአባ ባሕርይ መድረክ” ድረ-ገጽ ነው። መድረኩ በፖለቲካ ገለልተኛ የሆኑ ምሁራንና ባለሟያዎች ያቋቋሙት ሲሆን ዓላማውም በአማራው ብሎም በኢትዮጵያ ሃገረ-መንግስት ላይ ለወደቁት የኅልውና አደጋዎች ለሚዋደቁ ወገኖቻችን የቀውሱ መፍትሄዎችን በጥናት በማፍለቅ ምክረ-ሃሳብ ማቅረብ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓለም-አቀፍ ስምምነቶች የጸደቁ መብቶቹንና የሕግ የበላይነት እንዲከበሩለት የተቻለንን ድጋፍ መስጠት ትኩረታችን ነው። ግዴታችንም ነው። ከዚህም አልፈን የበለፀገችና በዲሞክራሲያው ስርዓት የዜጎች ሙሉ ነፃነቶች የሚከበሩባት፣ ግዴታዎችም የሚተገበሩባት የተባበረች ኢትዮጵያን ማዘመን ትልቅ ሞኞታችን ነው። 

 

ድረ-ገጻችን ስለእኛ ተልዕኮና ተግባራት፣ የተለያዩ አማራ-ተኮርና ኢትዮጵያ-ተኮር ሲቭክ ድርጅቶች የሚያወጧቸውን መግለጫዎችና ሰነዶች፣ እንዲሁም ለነውጥ-አልባ ትግል ጠቃሚ የመሰሉንን መጣጥፎች ያካትታል። ተመላልሳችሁ ጎብኙን። 


የዐማራ ሕዝብ በልጉቹ መስዋዕትነት ኅልውናውን አስከብሮ አርነቱን በዘላቂነት ይጎናጸፋል!!

የሁላችንም ቤት ብሄረ-ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፣ ትኖራለችም!!



Major Documents:

1.       An Amara Roadmap to Victory | የዐማራ የድል ፍኖተ ካርታ  (አ.ባ.መ.)  (September 2025)

2.       የሕዝባዊ እምቢተኝነት ስልት ለኢትዮጵያ  |  Civil Disobedience Strategy  (አ.ባ.መ.)

3.       Amara Freedom Charter | የዐማራ ኅልውና ቃል-ኪዳን  (አ.ባ.መ.)

4.       የአማራውን የኅልውና ንቅናቄ ለሚደግፉ ሚዲያዎች የሚረዳ የተግባቦትና መርህ  (አ.ባ.መ.)

5.       A Citizen-Centered Roadmap for Systemic  Political Transition in Ethiopia, Parts 1 and 2 |  ኢትዮጵያ፦ ዜጋ-ተኮር ፍኖተ-ካርታ ለፖለቲካ ስርዓት ለውጥ  (2025, ኢ.ሕ.ማ.ጉ.)